AMEA

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት ከአለም አቀፉ አሚአ ፓወር ኩባንያ ጋር ተስማምታለች፡፡ ስምምነቱ በዱባይ ከአራት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ እና አሚአ ኩባንያ ሀላፊዎች መካከል ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ለሚገነባዉ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማልማት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ከተሰማራው እና መቀመጫዉን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ካደረገዉ ከአሚአ ፓወር ጋር ስምምነት አድርጓል። በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት አመንጭቶ ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው። በኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን ለማልማት እና ለማንቀሳቀስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት እና የትግበራ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወቀው…
Read More