28
Aug
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀይል የማመንጨት አቅም በዕጥፍ ጨምሯል ተብሏል ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደጓን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል። ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያመነጩ ቆይተዋል፡፡ ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል እንደሚያመነጩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ይህ የአፍሪካ ትልቁ ግድብ በ2014 ዓ.ም ላይ…