28
Feb
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኬንያ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በናይሮቢ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ሲገለጽ የተለያዩ ተቋማትንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ኬንያ ሲጓዙ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ70 ዓመት በፊት ጀምሮ ጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ከአንድ ሳምንት በፊትም የኢትዮ ኬንያ ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ አካሂደዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ያለ ቪዛ ወደ ኬንያ እንዲሁም ኬንያዊያን ወደ ኢትዮጵያ ያለቪዛ እንዲገቡ የሚፈቅድ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ…