የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

ከድርቅ ጀምሮ እስከ በርሃማነት በተደቀነባት የአፍሪካ አህጉር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ የሚመክር የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል።

በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ይካሄዳልብተብሏል።

በጉባኤው ላይ ከ20 ቡላይ የአፍሪካ መሪዎች፣ የበርካታ ሀገራት ሚንስትሮች፣ ልዑኮችና የአየር ንብረት ተሟጋቾች ይሳተፋሉ።

በአህጉሪቱ እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ ባሉ ሀገራት ከ40 ዓመታት ወዲህ የከፋ የተባለ ድርቅ ተከስቷል።

በዚህም በአፍሪካ ቀንድ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትና ቀውስ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚለው እየጨመረ ከመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ አደጋዎች ሀገራት በየዓመቱ ከሰባት እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብታቸውን ያጣሉ።

የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ካልተቻለ የሚያደርሰው ጉዳት በ2030 ወደ 50 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል ተብሏል።

በጉባኤው የአፍሪካ መሪዎች ከአየር ንብረት ለውጥ በፍጥነት ማገገምና መቋቋም የሚስችሉ ጥረቶችን ይደግፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አያሌ ባለድርሻ አካላት በጉባኤው መፍትሄና እርምጃ ላይ የሚያተኩሩ ውሳኔዎች እንዲወሰኑ እየወተወቱ ሲሆን፤ ይህንም አቅፏል የተባለው “የናይሮቢ መግለጫ” በጉባኤው የመጨረሻ ቀን እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም ኮፕ28 የፊታችን ታህሳስ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ዱባይ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

አፍሪካ ከበለጸጉ ሀገራት ኢንዱስትሪዎች በሚለቀቁ በካይ ጋዝ እየተጎዳች ሲሆን በዱባይ በሚካሄደው ኮፕ28 ጉባኤ ላይ የበለጸጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ምዝገባ እና ካሳ መክፈል የሚያስችሉ አሰራሮች እንደሚጸድቁ ይጠበቃል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *