Climatechange

በኢትዮጵያ በጎርፍ አደጋ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በጎርፍ አደጋ አንድ ሚሊዮን ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በጎርፍ አደጋ ምክንያት አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሠዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ ኢትዮጵያ ካሏት ሦስት ወቅቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና አራት ወራትን የሚይዘው የበልግ ወቅት በደቡብ አጋማሽ ለሚገኙ የአገሪቱ አካባቢዎች ዋነኛ የዝናብ ወቅት ነው። ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉትን ወራቶችን በሚሸፍነው የበልግ ወቅት ለሶማሌ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ለደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች 55 በመቶ የዝናብ ስርጭታቸውን በዚህ ወቅት ያገኛሉ። የበልግ ወቅት ለምስራቅና ደቡብ ትግራይ፣ ለሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ለአማራና ኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ እንዲሁም አዲስ አበባን ጨምሮ ለመካከለኛው የአገሪቱ አካባቢ፣ ለምስራቅ አካባቢዎች (ሀረርና ድሬዳዋ) ሁለተኛ የዝናብ ወቅት ተደርጎ ይወሰዳል። የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም. የበልግ ወቅት በተለይም ዋነኛና…
Read More
በአፍሪካ በየአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በየ ዓመቱ 250 ሺህ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተገለጸ

በአፍሪካ በየአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በየ ዓመቱ 250 ሺህ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተገለጸ

የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ከዓለም ጤና ድርጅት ፣ አፍሪካ ጤና እና ጥናት ፋውንዴሽን፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና  ሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ፍትህ ጥምረት ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሚቲካ ምዌንዳ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥ ዜጎችን ለተደራራቢ የጤና ችግሮች እየዳረገ ነው ብለዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆች ለአየር ወለድ፣ ውሃ ወለድ፣ ለምግብ እጥረት እና ሌሎች የጤና ችግሮች እየዳረገ ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚው ጉዳቱን ለመቀነስ የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡…
Read More
ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር የስድስት ወራት ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ አለሙ ስሜ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለፓርላማው እንደተናገሩት፥ ነዳጅ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅማጥቅ ሆነ ለሌላ አላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገውን እገዳ በጥብቅ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ውሳኔው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ስጋቶች እና ከባህላዊ የነዳጅ ፍጆታ ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለሚመጣው ወጭ ስልታዊ ምላሽ ነውም ተብሏል። እየጨመረ የመጣው የነዳጅ ወጪ ፖሊሲ አውጪዎች አገሪቱ በተለመዱት ተሽከርካሪዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት እንዲገመግሙ እና የካርበን በካይ ጋዝ መጠንን ለመቀነስ ከሚደረገው…
Read More
ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

በአዲስ አበባ ከፍተኛ ጭስ የሚለቅ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ተሸከርካሪዎች የሚለቁትን ጭስ የሚለካ መሳሪያ እና ጥራት ማስጠበቂያ ወይም ስታንዳርድ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ እንደተናገሩት የመኪና ጭስ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው የተባለ ሲሆን እያንዳንዱ መኪና የሚያስወጣው ጪስ ይለካል ተብሏል። መኪናው ከተቀመጠው መለኪያ በላይ ጪስ የሚያመነጭ ከሆነ አገልግሎት እንዳይሰጥ ይደረጋል ብለዋል። አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ከተመረቱ 23 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ናቸው ያሉት ኃላፊው፤ ስለዚህ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ከአሁኑ መፍትሄ ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል። በመዲናዋ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ በርካታ መኪኖች መኖራቸውን…
Read More
የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

ከድርቅ ጀምሮ እስከ በርሃማነት በተደቀነባት የአፍሪካ አህጉር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ የሚመክር የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል። በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ይካሄዳልብተብሏል። በጉባኤው ላይ ከ20 ቡላይ የአፍሪካ መሪዎች፣ የበርካታ ሀገራት ሚንስትሮች፣ ልዑኮችና የአየር ንብረት ተሟጋቾች ይሳተፋሉ። በአህጉሪቱ እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ ባሉ ሀገራት ከ40 ዓመታት ወዲህ የከፋ የተባለ ድርቅ ተከስቷል። በዚህም በአፍሪካ ቀንድ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትና ቀውስ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚለው እየጨመረ ከመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ አደጋዎች ሀገራት በየዓመቱ ከሰባት እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብታቸውን ያጣሉ። የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ካልተቻለ…
Read More
የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ

የአፍሪካ ምግብ ዋስትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ

19ኛው የአፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች ጉባኤ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት እድሎችን መጠቀም እና ትብብርን ማጎልበት" በሚል ሀሳብ በአዲስ አቡባ ተካሂዷል። በዚህ ጉባኤ ላይ አፍሪካ አካባቢ ጥበቃ ሚንስትሮች፣ የዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓመታዊ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አዘጋጅ ሀገር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሱልጣን አልጃቢር ተገኝተዋል። እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት መሪዎች እንደተገኙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን የምግብ ዋስትና እየፈተነ ነው ብለዋል። አቶ ደመቀ አክለውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ አረንጓዴ አሻራ ስትራቴጂ ነድፋ እየተገበረች መሆኗንም ጠቅሰዋል። የኮፕ28 አለም አቀፍ አየር…
Read More
ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች

ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች

ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር በ 83 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፋል። ዶ/ር ተወልደብርሃን በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለችው ‹‹አዲ-ስላም›› የተሰኘች የገጠር መንደር  የተወለዱ ሲሆን ፣ በቀለም ትምህርት ገፍተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1955 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ የሁለተኛ እና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም ያላቸው ዶክተር ተወልደ በዘርፉ ላደረጉት ምርምርና በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲፈጠር ላደረጉት ጥረት በ2000 Right Livlihood Award ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ2006 ዓመት የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን Champions of the Earth ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…
Read More