Floods

በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ አብዛኞቹ ቦታዎች ቀጣዮቹ ቀናት የበልግ ዝናብ በአብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ላይ ይጠናከራል ተብሏል፡፡ በመጪዎቹ 10 ቀናት የበልግ ዝናብ በአብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከረና እየተስፋፋ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ይህን ተከትሎም በበልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም አስታውቋል። በተጨማሪም በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዮሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ምስራቅ ሸዋ፣ አዲስ አበባ፣ ምስራቅ አማራ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና አይሻ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቅሷል። ከኦሮሚያ ክልል የቄለም ወለጋ፣ የምዕራብ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉአባቦር፣ ጅማ፣ ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ…
Read More