13
Jan
ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ጸደቀ መመሪያው በመንገዶች ግራና ቀኝ በየ50 ኪሎሜትር ልዩነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሙላት የሚችል ፈጣን ቻርጀር ጣቢያ ማቋቋም ይፈቅዳል፡፡ ይሁንና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል ማቅረብ የሚፈልጉ ተቋማት ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ፈቃድ በመውሰድ እንዳለባቸው መመሪያ ይገልጻል። በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ የኤሌክትሪክ ሃይል መሙያዎች ከባለስልጣኑ ፈቃድ ማግኘት እንደሚጠበቅባቸው ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን በግል በቤት ውስጥ ከሚተከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሃይል መሙሊያ ማሽኖች ፈቃድ መጠየቅ የማይጠበቅባቸው መሆኑን ያመላከተው የተቋሙ መረጃ ከዚህ ውጭ ግን ማናቸውም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሃይል ሙሌት የሚሰጡ ማሽኖች መትከል የሚቻለው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑንም አመላክቷል። መመሪያው ለህዝብ በሽያጭ የኤሌክትሪክ ሃይል ሙሊት አገልግሎት የሚሰጡ ታሪፋቸው በባለስልጣኑ ሲጸድቅላቸው…