16
Dec
ውድድሩ የኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥ ትብብር፣ኢንፉሌንሰርስ እና ቬንደንስ የተሰኙ ተቋማት በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡ ሶስቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩት ተቋማት ከሁለት ወራት በፊት ወጣቶች በደን አጠባበቅ ዙሪያ በኢሴይ ራይቲንግ፣ ኢንፎ ግራፊ እና ቪዲዮ የታገዘ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ የኢንፉሌንሰርስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ናሆም ፈቃዱ እንዳሉት በተደረገው ማስታወቂያ መሰረት 80 ወጣቶች በውድድሩ ላይ እንደተሳተፉ ተናግረዋል፡፡ ከሁሉም ተወዳዳሪዎች ውስጥ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የወጡ ወጣት አሸናፊዎች ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር ሽልማት ተሸልመዋል፡፡ ወጣት ናሆም እንዳሉት ተቋማቸው ኢንፉሌንሰርስ ሁሉም ሰው ለአካባቢ ጥበቃ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በሚል መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡ ለአካባቢ ጥበቃ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ለሚፈልጉ ሰዎች ነው የተቋቋመው፣የአየር ንብረት ለውጥ የባሰ ጉዳት የሚያደርሰው…