Biodiversity

ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

የጣና ሀይቅ ደሴትና ገዳማት በአለም አቀፍ የቅርስ መዝገብ እንዲሰፍሩ የሚያስችለዉ ሰነድ ለዮኔስኮ ተልኳል። በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  አስታውቋል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ እምቢአለ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ በርካታ የመስህብ ቦታዎች እንደመኖራቸው የጣና ሀይቅ እና አካባቢውን በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም  የጣና ሀይቅ ደሴቶች በብዛ ህይወት ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ይህ ስፍራ በአለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ሰነድ ዙሪያ ማስተካከያ መደረጉን ተናግረዋል። ሰነዱን አስመልክቶ አስተያየት የመስጠትና ተጨማሪ ግብዓቶችና ማስተካከያዎችን የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ እንደቆየ የገለፁት…
Read More
የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

ከ125 ዓመት በፊት የተመሰረተው የጀርመኑ የተፈጥሮ እና ብዝሀ ህይወት ጥበቃ ተቋም (ናቡ) የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡ የናቡ ፕሬዝዳንት ጆርግ አንድሪያስ ክሩገር እንዳሉት ኢትዮጵያ የብዝሃ ህይወት ሀብት በብዛት ከሚገኙባቸው ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ እና ከአፍሪካ ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መግቢያ በመሆኗ ቢሯቸውን በአዲስ አበባ ለመክፈት እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት በማቀላጠፍ ተጨማሪ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራዎችን ለማስራት ቢሯችንን በአዲስ አበባ ለመክፈት አነሳስቶናልም ብለዋል፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው ይህ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ተቋም በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ7 ሀገራት ላይ እየሰራ…
Read More