NABU

የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

ከ125 ዓመት በፊት የተመሰረተው የጀርመኑ የተፈጥሮ እና ብዝሀ ህይወት ጥበቃ ተቋም (ናቡ) የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡ የናቡ ፕሬዝዳንት ጆርግ አንድሪያስ ክሩገር እንዳሉት ኢትዮጵያ የብዝሃ ህይወት ሀብት በብዛት ከሚገኙባቸው ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ እና ከአፍሪካ ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መግቢያ በመሆኗ ቢሯቸውን በአዲስ አበባ ለመክፈት እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት በማቀላጠፍ ተጨማሪ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራዎችን ለማስራት ቢሯችንን በአዲስ አበባ ለመክፈት አነሳስቶናልም ብለዋል፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው ይህ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ተቋም በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ7 ሀገራት ላይ እየሰራ…
Read More