plasticbottles

ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርቶች መጠቀምን የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርቶች መጠቀምን የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፕላስቲክ ምርቶች አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚጥል ረቂ ህግ ላይ ተወያይቷል፡፡ ምክር ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ለአንድ ጊዜ ግልጋሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅን አዘጋጅቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለዝርዝር እይታ እና ተጨማሪ ግብዓት ታክሎበት እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። ረቂቅ አዋጁ የሀገሪቱን የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ ማጓጓዝ፣ ክምችት፣ መልሶ አጠቃቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት ማስያዝ ላይ ያተኮረ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ በበኩላቸው ለሀገሪቱ ፓርላማ የተመራው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤…
Read More