Oldvehicles

ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ በካይ ጋዝ የሚቆጣጠር መመሪያ ተዘጋጀ

ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ በካይ ጋዝ የሚቆጣጠር መመሪያ ተዘጋጀ

‎በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው፤ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣን ጎጂ የካይ ጋዝ ልቀት ለመቆጣጠር የሚያገለግለው አስገዳጅ መመሪያ ከመስከረም 30 ቀን 2018 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ዋነኛ ዓላማው የትራንስፖርት ዘርፉ ለበካይ ጋዝ ልቀት የሁለት ሦስተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ በጎጂ በካይ ጋዞች ምክንያት የሚከሰትን የአየር ብክለት መቀነስ ሲሆን፤ አዲሱ መመሪያ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር ተሽከርካሪዎች ወደ አየር የሚለቁትን የበካይ ጋዝ መጠን የሚቆጣጠር መሳሪያ እንዲገጥሙ ይገደዳሉ ተብሏል። የተቋሙ የትራንስፖርት ዘርፍ የአየር ንብረት ክትትል እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ግርማ ሳሙኤል፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መመሪያው ከጸደቀበት መጋቢት 2017 ጀምሮ ውይይቶች ሲካሄዱበት እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህም አስገዳጅ መመሪያው ከጸደቀ በኋላ ከታክሲ ማኅበራት፣ ከክልል ከተማ አስተዳደሮች…
Read More
ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ልታግድ መሆኗን ገለጸች

በአዲስ አበባ ከፍተኛ ጭስ የሚለቅ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ተሸከርካሪዎች የሚለቁትን ጭስ የሚለካ መሳሪያ እና ጥራት ማስጠበቂያ ወይም ስታንዳርድ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ እንደተናገሩት የመኪና ጭስ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው የተባለ ሲሆን እያንዳንዱ መኪና የሚያስወጣው ጪስ ይለካል ተብሏል። መኪናው ከተቀመጠው መለኪያ በላይ ጪስ የሚያመነጭ ከሆነ አገልግሎት እንዳይሰጥ ይደረጋል ብለዋል። አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ከተመረቱ 23 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ናቸው ያሉት ኃላፊው፤ ስለዚህ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ከአሁኑ መፍትሄ ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል። በመዲናዋ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ በርካታ መኪኖች መኖራቸውን…
Read More