Fuel

ኢትዮጵያ ከሚያዚያ ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ እንደምታነሳ ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሚያዚያ ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ እንደምታነሳ ገለጸች

ኢትዮጵያ የየነዳጅ ፍላጎቷን ሙሉ ለሙሉ ከውጭ ሀገራት በመግዛት የምትሸፍን ሲሆን የትራንስፖርት ዋጋ እንዳያንር በሚል የነዳጅ ድጎማ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ የመንግስት ወጪ በመጨመሩ እና የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት የነዳጅ ድጎማን ቀስ በቀስ ለመቀነስ እና ለማቆም እንደወሰነች የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባሳለፍነው ዓመት ይፋ አድርጓል፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማይሰጡ ድርጅቶች የነዳጅ ድጎማው ከቆመ አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን አሁን ደግሞ የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችም የነዳጅ ድጎማ እንደማያገኙ ተገልጿል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን  2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች…
Read More
ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር የስድስት ወራት ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ አለሙ ስሜ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለፓርላማው እንደተናገሩት፥ ነዳጅ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅማጥቅ ሆነ ለሌላ አላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገውን እገዳ በጥብቅ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ውሳኔው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ስጋቶች እና ከባህላዊ የነዳጅ ፍጆታ ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለሚመጣው ወጭ ስልታዊ ምላሽ ነውም ተብሏል። እየጨመረ የመጣው የነዳጅ ወጪ ፖሊሲ አውጪዎች አገሪቱ በተለመዱት ተሽከርካሪዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት እንዲገመግሙ እና የካርበን በካይ ጋዝ መጠንን ለመቀነስ ከሚደረገው…
Read More
ኢትዮጵያ ለ2016 ነዳጅ ግዢ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ኢትዮጵያ ለ2016 ነዳጅ ግዢ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት ማቀዷን አስታውቃለች። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንዳስታወቀው ለ2016 ዓ/ም ወደ አገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ። ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ለማስገባት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ " ቪቶል " የተባለው የባህሬን ኩባንያ በድጋሚ በማሸነፉ የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2016 ዓ.ም. ለማስገባት ያቀደውን ሙሉ ለሙሉ ቤንዚን፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የነጭ ናፍጣ ግዥ 40 በመቶውን " ቪቶል " ኩባንያ እንደሚያስገባ ታውቋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ለ1 ዓመት የሚያስፈልገውን 760 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ኩባንያው ያቀርባል ተብላል፡፡…
Read More