01
Apr
ኢትዮጵያ የየነዳጅ ፍላጎቷን ሙሉ ለሙሉ ከውጭ ሀገራት በመግዛት የምትሸፍን ሲሆን የትራንስፖርት ዋጋ እንዳያንር በሚል የነዳጅ ድጎማ ስታደርግ ቆይታለች፡፡ የመንግስት ወጪ በመጨመሩ እና የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት የነዳጅ ድጎማን ቀስ በቀስ ለመቀነስ እና ለማቆም እንደወሰነች የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባሳለፍነው ዓመት ይፋ አድርጓል፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማይሰጡ ድርጅቶች የነዳጅ ድጎማው ከቆመ አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን አሁን ደግሞ የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችም የነዳጅ ድጎማ እንደማያገኙ ተገልጿል፡፡ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ ሲደረግላቸው የነበሩ የሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ድጎማው እንደሚቋረጥ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። መንግሥት ለረጅም ጊዜ ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ መጠን የለው ድጎማን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ ይህንን ለማስቀረት በሂደት የነዳጅ ምርቶች…