Vitol

ኢትዮጵያ ለ2016 ነዳጅ ግዢ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ኢትዮጵያ ለ2016 ነዳጅ ግዢ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልጋት ገለጸች

ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት ማቀዷን አስታውቃለች። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንዳስታወቀው ለ2016 ዓ/ም ወደ አገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ። ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ለማስገባት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ " ቪቶል " የተባለው የባህሬን ኩባንያ በድጋሚ በማሸነፉ የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2016 ዓ.ም. ለማስገባት ያቀደውን ሙሉ ለሙሉ ቤንዚን፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የነጭ ናፍጣ ግዥ 40 በመቶውን " ቪቶል " ኩባንያ እንደሚያስገባ ታውቋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ለ1 ዓመት የሚያስፈልገውን 760 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ኩባንያው ያቀርባል ተብላል፡፡…
Read More