22
Apr
የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ከዓለም ጤና ድርጅት ፣ አፍሪካ ጤና እና ጥናት ፋውንዴሽን፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የፓን አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ፍትህ ጥምረት ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሚቲካ ምዌንዳ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥ ዜጎችን ለተደራራቢ የጤና ችግሮች እየዳረገ ነው ብለዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆች ለአየር ወለድ፣ ውሃ ወለድ፣ ለምግብ እጥረት እና ሌሎች የጤና ችግሮች እየዳረገ ነው ያሉት ስራ አስፈጻሚው ጉዳቱን ለመቀነስ የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡…