Zanzibar

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጃል መሮ ፊት ለፊት ተገናኙ

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪው ጃል መሮ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመራቸው ተሰምቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር የተካሄደውን ድርድር የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና ኬንያ አስተባባሪ እና አሸማጋይ ሚና መውሰዳቸው ይታወሳል። አሁን የተጀመረውን ንግግር ማን እንደሚያደራድር ግልጽ ባይሆንም፣ ኢጋድ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሚና ሳያስቀጥል እንዳልቀረ ተጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ…
Read More
የፌደራል መንግሥት እና ኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ድርድር አለመሳካቱ ተገለጸ

የፌደራል መንግሥት እና ኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ድርድር አለመሳካቱ ተገለጸ

የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቋል ብሏል። ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ነው ያለው ሚንስቴሩ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ አልተደረሰም ብሏል። ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ እንደተግባቡ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ መርሖች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም እንዳለው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ይህንን መልካም አጋጣሚና በውይይት ችግሮችን የመፍታት በጎ ጅምር በመጠቀም ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ፅኑ አቋም እንዳለው አስታውቋል። አሜሪካ በታንዛኒያ ራስ…
Read More
መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር እየተደረገ ስላለው ድርድር መረጃ እንዲሰጥ ተጠየቀ

መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር እየተደረገ ስላለው ድርድር መረጃ እንዲሰጥ ተጠየቀ

መንግሥት ‹‹ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› ጋር ስለሚያደርገው ድርድር በቂ መረጃ ይስጥ ሲል ኢዜማ አሳስቧል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መንግሥት ራሱን ‹‹የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር ስለሚያደርገው ድርድር በቂ መረጃ ይስጥ ሲል ጠይቋል፡፡  ፓርቲው በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ሲገደሉ ንብረታቸውም ሲወድምና ከቀያቸው ሲፈናቀሉ በግልጽ ተመልክተናል ብሏል፡፡ መንግስትም በተደጋጋሚ የተፈፀሙትን በደሎች ይህ ታጣቂ ቡድን ሲፈፅማቸው እንደነበር ከማሳወቁ አንፃር ይህን መሰል የዜጎች ሰቆቃ የሚያስቆም ድርድር ውስጥ መግባቱን ፓርቲው እንደሚደግፈው ገልጿል፡፡  ይሁንና ብልጽግና ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረበትን ጊዜ ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያየ ጊዜ የሚፈጸሙ ድርድሮች ግልጽነት የጎድላቸው እና አፈፃፀማቸው ደካማ መሆናቸውን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ለአብነትም ከሕወሓት…
Read More