07
Mar
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት በታንዛንያ ይፋዊ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዳሬሰላም ቆይታቸው የአቪዬሽን እና ኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ስምምነት ከፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሐሰን መንግስት ጋር መፈጸማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በሰጡት ሳምንታዊ የዲፕሎማሲ መግለጫ ለይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለታንዛንያ 400 ሜጋዋት ሀይል ለመሸጥ ስምምነት ፈጽማለች ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በተያዘው ዓመት ከሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ሶስት ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ 182 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዷም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ለጅቡቲ፣…