01
Jul
ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ማደራደር መጀመሯ ተገልጿል። ሬውተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው ድርድሩ በቱርክ መዲና አንካራ በመካሄድ ለይ ይገኛል። ይሁን እንጂ አደራዳሪዋ ቱርክም ሆነች ተደራዳሪዎቹ እስካሁን ማረጋገጫ አልሰጡም። የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሙአሊም ፊቂ የመሩት ልኡክ በትናንትናው እለት ወደ ቱርክ ማቅናቱን ቢዘግቡም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣንም በአንካራ ተጀምሯል ስለተባለው ድርድር ምንም መናገር አንፈልግም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊላንድ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጥር ወር ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው የወደብ ስምምነት ምክንያት የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።…