02
May
መንግሥት ‹‹ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› ጋር ስለሚያደርገው ድርድር በቂ መረጃ ይስጥ ሲል ኢዜማ አሳስቧል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መንግሥት ራሱን ‹‹የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት›› ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር ስለሚያደርገው ድርድር በቂ መረጃ ይስጥ ሲል ጠይቋል፡፡ ፓርቲው በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ሲገደሉ ንብረታቸውም ሲወድምና ከቀያቸው ሲፈናቀሉ በግልጽ ተመልክተናል ብሏል፡፡ መንግስትም በተደጋጋሚ የተፈፀሙትን በደሎች ይህ ታጣቂ ቡድን ሲፈፅማቸው እንደነበር ከማሳወቁ አንፃር ይህን መሰል የዜጎች ሰቆቃ የሚያስቆም ድርድር ውስጥ መግባቱን ፓርቲው እንደሚደግፈው ገልጿል፡፡ ይሁንና ብልጽግና ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረበትን ጊዜ ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያየ ጊዜ የሚፈጸሙ ድርድሮች ግልጽነት የጎድላቸው እና አፈፃፀማቸው ደካማ መሆናቸውን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ለአብነትም ከሕወሓት…