Debts

ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ክፍያ አለመፈጸሟ ተገለጸ

ሱዳን ለኢትዮጵያ መክፈል ያለባትን የኤሌክትሪክ ክፍያ ባለመክፈሏ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል። ሱዳን ከኢትዮጵያ ለምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ በየወሩ ሙሉ ለሙሉ መክፈል ቢኖርባትም ካለፈው ዓመት ጀምሮ ክፍያዋን በማቆረጧ፣ ተከፍሎ ያላለቀና መጠኑ ያልተገለጸ በርካታ ሒሳብ እንዳለባት ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለሦስት የጎረቤት አገሮች የኤሌክትሪክ ኃይል ትልካለች። ሀገሮቹም አንደኛው ወር ሲጠናቀቅ የሚቀጥለው ወር ላይ ሆነው ባለፈው ወር ለተላከው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ክፍያ ይፈጽማሉ። ሱዳንም በእንዲህ ዓይነት አሠራር መክፈል የነበረባትን ቢሆንም ክፍያ አየቆራረጡ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን ጨርሰው እየከፈሉና እያጠናቀቁ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ተናግረዋል። "የአንድ ወር ሙሉ የሚከፈልበት፣ ሌላው ሙሉውን የማይከፈልበት፣ አልያም ደግሞ በከፊል ከሌሎች ክፍያዎች ጋር እያደረጉ…
Read More