Foodaid

ብሪታንያ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለማቅረብ የ125 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ብሪታንያ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለማቅረብ የ125 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

የብሪታንያ የአፍሪካ ልማት ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከጉብኝቱ በኋላ ድጋፉን አድርገዋል ተብሏል። ሚንስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ እንዳሉት አሳሳቢ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር በቀጣይ ወራት 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ይደርሳክ ብለዋል። የ125 ሚሊየን ዶላር ድጋፉ ለሶስት ሚሊየን ሰዎች ህይወት አድን እርዳታ ለማቅረብ እንደሚውልም ተገልጿል። አስቸኳይ ድጋፉ በአልሚ ምግብና ሌሎች ወሳኝ ግብአቶች ምክንያት እየተከሰተ የሚገኘውን ሞት ለመቀነስ ለ75 የጤና ተቋማት የተለያዩ ድጋፎችን ለማቅረብ ነውም ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት ከአንድ ወር በፊት በኢትዮጵያ በድርቅ እና ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል። በኢትዮጵያ በጦርነት እና ድርቅ ምክንያቶች ለእርዳታ የሚዳረጉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ በመምጣት ላይ ይገኛል።…
Read More