Dullamekonnen

አቶ ዱላ መኮንን የዳሸን ባንክ ቦርድ ሊቀ-መንበር ሆነው ተመረጡ

አቶ ዱላ መኮንን የዳሸን ባንክ ቦርድ ሊቀ-መንበር ሆነው ተመረጡ

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 30ኛው መደበኛ ጉባኤ የተመረጠውና የምርጫውም ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፀደቀለት አዲሱ የዳሸን ባንክ ቦርድ ባደረገው የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት ያገለገሉትን አቶ ዱላ መኮንንን በድጋሚ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት መርጧል፡፡  አዲሱ ቦርድ የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄደው ጉባኤ ለቀጣይ ሶስት አመታት ዳሸን ባንክን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበርነት እንዲያገለግሉ በድጋሜ የመረጣቸው አቶ ዱላ መኮንን በአሁኑ ወቅት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡  አዲሱ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ፣ እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪያቸውንም በቢዝነስ አስተዳደር ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡…
Read More