09
Dec
የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኄኖክ ከበደ ከሓላፊነታቸው ተነሱ የአማራ ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሔኖክ ከበደ ባንኩን ለ460 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ዳርገዋል በሚል ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ ባንኩ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው በተጨማሪም የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ የአፈጻጸም ድክመት አሳይተዋል በሚል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር መላኩ ፈንታ ፊርማ ከሓላፊነታቸው አንሥቷል። የባንኩ ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ኹለቱም ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ፣ በየጊዜው በሚሳዩት የሥራ አፈጻጸም ድክመት፣ የባንኩን ስትራቴጂያዊ ግቦች እና ቁልፍ የአፈጻጸም መመዘኛዎችን ማሳካት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ባንኩ በ2014/15 ዓ.ም. ከ306 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማስመዝገብ ዐቅዶ የነበረ ቢኾንም፣ ብር 460,286,000 ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በሌላቸው ሥልጣን ባሳለፉት አስተዳደራዊ…