13
Sep
ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጤና እክል ምክንያት ከሃላፊነት የለቀቁት ዮሀንስ አያሌው ብሩ (ዶ/ር)፣ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸመዋል፡፡ የአማራ ባንክ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ እንዳጋራው ዩሀንስ አያሌው ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ስራ አስፈጻሚነት መሾማቸውን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ በሰባት ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ከሁለት ዓመት በፊት ስራ የጀመረው የአማራ ባንክ 138 ሺህ ባለ አክስዮኖች የመሰረቱት የግል ባንክም ነው፡፡ ዮሐንስ አያሌው በልማት ባንክ የስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም…