EnatBank

እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ አገር አቀፍ ጽሑፍ ውድድር  ጀመረ

እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ አገር አቀፍ ጽሑፍ ውድድር  ጀመረ

እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ ኹሉንም የማኅበረሰብ ክፍል የሚያሳትፍና የሚያሽልም አገራዊ የጽሑፍ ውድድር መጀመሩን አስታውቋል። የባንኩ ማርኬቲንግ እና ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አክሊል ግርማ እንዳሉት "ውድድሩ እናት ባንክ ከተመሠረተበት ራዕይና ተልዕኮ አንፃር የሚዛመድ ብሎም የባንኩን ማኅበራዊ እሴት ማዕከል የሚያደርግ አገር አቀፍ መርሐ ግብር ነው" ብለዋል። አቶ አክሊል አክለውም ባንኩ ለዘመናት ለአገርም ሆነ ለቤተሰብ ምሰሶ ለሆኑት የኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ለአንድ ወር የሚቆይ ሽልማት የሚያስገኝ፣ “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል። ውድድሩ በዋናነት ኹሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርዝር ጽሑፍ ማለትም ግጥም ባልሆነ በወግ መልክ ወይንም በደብዳቤ ቅርፅ የሚገልጽበትና “ለእናት" የሚልበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ጨምረው አስረድተዋል። "ኹሉም…
Read More