KCB

የኬንያው ኬሲቢ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ድርሻ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ

የኬንያው ኬሲቢ ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ድርሻ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ

ዋና መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገው ኬሲቢ ግሩፕ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ወደ ገበያው ለመግባት አማራጮችን እየገመገመ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ባንክ የሆነው ኬሲቢ ኬንያን ጨምሮ በቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛንያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በባንክ ኢንዱስትሪ እየሰራ ይገኛል። ይህ ባንክ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ባንኮች የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት መወሰኑ ተሰምቷል። ይሁንና የኬንያው ባንክ ከየትኛው የኢትዮጵያ ባንክ አክስዮን ለመግዛት እንደወሰነ አልታወቀም። የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክተር የሆኑት ላውረንስ ኪማቲ ከቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ባንክ ገበያ ላይ ቅኝተ ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ከተለያዩ ባንኮች ሰዎች ጋር መወያየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ከእነርሱ ጋር ሊሠሩ የሚችሉትን መለየታቸውንም በቆይታቸው ተናግረዋል፡፡ እንደ ላውረንስ የባንኮቹ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የተሻለ…
Read More