15
Jul
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው 7ኛ ስብሰባው፣ የተለያዩ የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቦ ማጽደቁን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ያለመ አዳዲስና ወሳኝ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ማሳለፉን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል። ኮሚቴው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወሰኑንም ገልጿል። እስካሁን ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ ተጥሎ የነበረው የ24 በመቶ ቀጥተኛ የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል። በባንኮች ላይ የብድር ገደብ ውሳኔ ተጥሎ የነበረው ኢኮኖሚው በወለድ ምጣኔ ላይ ወደተመሠረተ የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት እስኪሸጋገር እንደነበር…