liquidity

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባበለ

በኢትዮጵያ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥማል መባሉን ብሔራዊ ባንክ አስተባብሏል። በኢትዮጵያ በተለይም የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው በተለያየ መልኩ ሲገለጹ ቆይቷል። የባንክ ደንበኞችም ለአገልግሎት ባመሩባቸው የግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ሲጠይቁ እንዳልሰጧቸው በርካታ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በስድስተኛው የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ እየተሰተፈ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል። የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ እንዳሉት "በኢትዮጵያ በግል ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል እሚባለው መረጃ ሀሰት ነው" ብለዋል። የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል የተባሉት አምስት ባንኮች ናቸው መባሉን ሰምተናል ፣ "ነገር ግን በሶስት ባንኮች ላይ የተወሰነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሞ ነበር፣ ብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቋማት በወሰዷቸው ማስተካከያዎች አሁን ላይ ከአንድ…
Read More