07
Apr
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ ከሚያቀርብ የቻይና ቴክስታይል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ አቅርቦት ከቻይናው ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል። የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለሠራተኞች እንዲቀርብ የሚያስችል ውይይት ከጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተመላክቷል፡፡ ለደንብ ልብስ አቅርቦቱ ባንኩ ከፍተኛ ወጪ በመመደብ ለአብዛኛው ሠራተኛ ወጪውን የሸፈነ ሲሆን፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ የተወሰነ ወጪ ተጋርተው የሚቀርብ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ የጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ጋዊ ቻንሁሀ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ደንብ ልብስ ተቋማቸው በኢትዮጵያ ቅርንጫፉ ከሚሰራቸው አቅርቦቶች ትልቁ…