13
Jul
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ሰነዶች ሽያጭን በይፋ አስጀምረዋል። የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚህ ጊዜ እንዳሉት መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የግምጃ ቤት ሰነዶችን ለገበያ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት ውስጥ መንግስት ከበጀተው 1.9 ትርሊዮን ብር ውስጥ 188 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት እንዳለበት ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ከገጠመው የበጀት ጉድለት ውስጥም 173 ቢሊዮን ብሩን ግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ በማቅረብ ለመሰብሰብ መታቀዱንም አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ብድሩ ከሰነድ ገዢዎች የሚሰበሰበው የዋጋ ግሽበትን በማያባብስና የማክሮ ኢኮኖሚውን በማያናጋ መልኩ እንደሚሆንም ገልጸው ነባር የግምጃ ሰነዶችን ወደ ኤሌክትሮኒክስ መንገድ ስራዎች እየተቀየሩ መሆኑን፣ አዳዲስ ግምጃ ሰነዶችም በዚህ መልኩ ለገበያ ይቀርባሉም…