Stockmarket

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ አዲስ መመሪያ አወጣ

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ አዲስ መመሪያ አወጣ

በአሁኑ ወቅት በካፒታል ገበያ ሥር በተለያዩ ዘርፎች አገልግሎት ለመስጠት 10 ተቋማት የፈቃድ ማመልከቻ አስገብተው እየተጠባበቁ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታውቋል። በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ኃላፊ አቶ እንድሪስ ሰልማን፤ በኢትዮጵያ ያለው የካፒታል ገበያ ገና በማደግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ከጊዜ ወደጊዜ ፍላጎቱ እየጨመረ እንደሚመጣ ገልጸው፤ ያንን ፍላጎት ለመሙላት የሚያስችል ተጨማሪ አገልግሎት ሰጪዎች ገበያውን ሊቀላቀሉ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል። በዚህም ወደ 10 ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ደግሞ አንድ ሰው የኢንቨስትመንትና የሰነደ መዋዕለ ነዋይ አማካሪነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፈቃድ ማመልከቻ በማስገባት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ያመለከተው አካል በሙሉ ፈቃድ ይሰጠዋል ማለት እንዳልሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ "በተቀመጠው የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ መስፈርት መሰረት…
Read More
መንግስት ከግምጃ ሰነድ ግዢዎች 173 ቢሊዮን ብር እንደሚሰበስብ ገለጸ

መንግስት ከግምጃ ሰነድ ግዢዎች 173 ቢሊዮን ብር እንደሚሰበስብ ገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ሰነዶች ሽያጭን በይፋ አስጀምረዋል። የገንዘብ ሚንስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚህ ጊዜ እንዳሉት መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የግምጃ ቤት ሰነዶችን ለገበያ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት ውስጥ መንግስት ከበጀተው 1.9 ትርሊዮን ብር ውስጥ 188 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት እንዳለበት ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ከገጠመው የበጀት ጉድለት ውስጥም 173 ቢሊዮን ብሩን ግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ በማቅረብ ለመሰብሰብ መታቀዱንም አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ብድሩ ከሰነድ ገዢዎች የሚሰበሰበው የዋጋ ግሽበትን በማያባብስና የማክሮ ኢኮኖሚውን በማያናጋ መልኩ እንደሚሆንም ገልጸው ነባር የግምጃ ሰነዶችን ወደ ኤሌክትሮኒክስ መንገድ ስራዎች እየተቀየሩ መሆኑን፣ አዳዲስ ግምጃ ሰነዶችም በዚህ መልኩ ለገበያ ይቀርባሉም…
Read More
ኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ገበያን ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም አስጀመረች

ኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ገበያን ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም አስጀመረች

ኢትዮጵያ በአጼ ሀይለስላሴ አስተዳድር ዘመን የስቶክ ግብይት የሚፈቅድ ስርዓት የነበራት ቢሆንም በደርግ ዘመን ተቋርጦ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከ50 ዓመት በኋላ የስቶክ ግብይትን ዳግም ያስጀመረች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አስጀምረዋል፡፡ በዚህ የግብይት ስርዓት መሰረት ኩባንያዎች አክስዮኖቻቸውን በይፋ ለገዢዎች መሸጥ የጀመሩ ሲሆን ሸማቾች ደግሞ ለሚገዙት አክስዮን ዋስትና የሚሰጥ ተቋምም ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ይህን የአክስዮን ግብይት የሚያሳልጡ ሁለት መንግስታዊ ተቋማት የተቋቋሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት እና የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የስቶክ ግብይትን ከአንድ ዓመት በፊት የመጀመር እቅድ የነበራት ቢሆንም ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር 39 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የመንግስት…
Read More