01
Dec
ባንኩ በግብርና ስራዎች ለተሰማሩ ተበዳሪዎች የብድር ወለድ መጠኑን ከ11 በመቶ ወደ 7 በመቶ ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል። ባንኩ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎችን ለማበረታታት በሚል ለተበዳሪዎች በሚሰጠው ብድር ላይ ያስከፍል በነበረው ወለድ ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የብድር ወለድ ቅናሽ የተደረገው ያ ያልታረሰን የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ አስታውቋል። በዚህም መሰረት በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል ብሏል። ልማት ባንክ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ለማሳደግ እና ከውጭ ተመርተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚል የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት…