chinaafrica

ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ የሚዘልቅ የነዳጅ መስመር ልገነባ ነው አለች

ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ የሚዘልቅ የነዳጅ መስመር ልገነባ ነው አለች

የተትረፈረፈ የነዳጅ ሀብት ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ደቡብ ሱዳን ከዚህ በፊት ነዳጇን በሱዳን በኩል አድርጋ ለዓለም ገበያ ስታቀርብ ቆይታለች፡፡ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መሆኗን ተከትሎ እስከ ፖርት ሱዳን የተዘረጋው የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በጦርነቱ ወድሞባታል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ የተዘረጋ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተገልጿል፡፡ በቻይና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሲሳተፉ የነበሩት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ የሚዘረጋ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ዙሪያ መክረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከቻይና ብሔራዊ ነዳጅ ኮርፖሬሽን ሃላፊ ዳይ ሁሊያንግ ጋር በቤጂንግ መምከራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ የቻይናው ነዳጅ ኮርፖሬሽን…
Read More