04
Jun
በጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ብሄረሰብ ታፍነው ለባርነት የሚወሰዱ ህፃናት መኖራቸውን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የሕገ ወጥ ዝውውር ጽህፈት ቤት አሰተባባሪ አቶ ኡቶው ቹሩ እንደተናገሩት በዚህ መልኩ የሚወሰዱ ህፃናትን የማስመለስ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ህገወጥ የህፃናት ዝውውርን ማስቀረት አልተቻለም ብለዋል። በደቡብ ሱዳን በኩል ያለው ድንበር ክፍት መሆን በክልሉ ያሉ እና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በህገወጥ መልኩ ለመውሰድ አመቺ እንዳደረገው ገልፀው ባለሀብቶች ህፃናቱን በከብት የሚለውጡበት ሁኔታ መኖሩም ድርጊቱን እንዳይቆም ማድረጉን ተናግረዋል። አኙዋክ ብሔረሰብ ዞንን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ህፃናቱ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከተወሰዱት ውስጥ በቅርቡ ሶስት ህፃናትን ማስመለስ መቻሉን የገለፁት አቶ ኡቶው በህይወት መኖራቸው ያልተረጋገጡ…