13
May
ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የላሙ ወደብን ለማልማት እና ለመጠቀም በ2001 ዓ.ም በወቅቱ የኬንያ ፕሬዝዳንት፣ ሞ ኪባኪ፣ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት አማካኝነት ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል፡፡ ኬንያ ይህን ፕሮጀክት በማልማት ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እንዲጠቀሙበት ፍላጎት ያላት ቢሆንም ኢትዮጵያ እስካሁን ፍላጎት እንዳልነበራት ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የገቢ ወጪ ንግድ አማራጭ ወደብ እንዲኖራት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ሲሆን የላሙ ወደብን አንዱ አማራጭ አድርጎ ለመጠቀም መወሰኑ ከወራት በፊት መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ ይህ ስምምነት ከተፈረመ ከ15 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የላሙ ወደብን መጠቀም ጀምራለች፡፡ "ዓባይ" የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ግንቦት 3 ቀን 2016…