18
Jul
ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በፓርላማ በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ የናይል ተፋሰስ አባል የሆኑ 11 ሀገራት በኡጋንዳ ኢንተቤ ባደረጉት ስምምነት የናይል ወንዝን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ነው፡፡ ስምምነቱ ከ11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ስድስት ሀገራት በፓርላማ ካጸደቁ ቋሚ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት ይችላል ተብሏል፡፡ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለጹት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከተፈረመ ቆይቷል፡፡ አምስት ሀገራት በፓርላማቸው አጽድቀው ነበር፡፡ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለመመስረት የሚጠበቀው ስድስተኛ ሀገር በፓርላማ እስኪያጸድቅ ድረስ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን አጸድቃለች ብለዋል፡፡ ስድስት ሀገራት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ማጽደቃቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ…