China

ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላከ የአህያ ስጋ 300 ሺህ ዶላር ማግኘቷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላከ የአህያ ስጋ 300 ሺህ ዶላር ማግኘቷን ገለጸች

ቻይና ዋነኛዋ የኢትዮጵያ አህያ ስጋ የተላከባት ሀገር ስትሆን ፍላጎቱ እያደገ እንደሆነም ተገልጿል። በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የአህያ ስጋን ወደ ሆንግኮንግ በመላክ 3 መቶ ሺህ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስትቲዩት አስታውቋል፡፡ በኢንስትቲዩቱ ምክትል ዋና  ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሳህሉ ሙሉ እንደተናገሩት፣ ከአህያ ስጋ ውጪ የአህያ ቆዳን እንደ ቻይና ያሉ ሃገራት ለመድሃኒትነት በስፋት ሲጠቀሙበት የሚስተዋል በመሆኑ የስጋ ምርቱን ወደ ሆንግኮንግ እንዲላክ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ገቢው  የተገኘውም በተጠናቀቀው በጀት አመት 140 ቶን የአህያ ስጋ ምርትን ወደ ውጪ ገበያ በመላክ እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በበጀት አመቱ 600 ቶን የአህያ ስጋን ወደ ውጪ ለመላክ አስቀድሞ ታቅዶ እንደነበር ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡ በአህያ ስጋ የወጪ ንግድ  ዙሪያ የቄራ ድርጅቶች…
Read More
ቴክኖ ሞባይል ካሞን 20 የተሰኘ ምርቱን ይፋ አደረገ

ቴክኖ ሞባይል ካሞን 20 የተሰኘ ምርቱን ይፋ አደረገ

ዋና መቀመጫውን ቻይና ያደረገው ቴክኖ ሞባይል አዲስ የሞባይል ምርቱን ለኢትዮጵያ ደንበኞቹ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል። ቴክኖ ሞባይል ይፋ ያደረገው ካሞን 20 አዲስ ምርት የአምስተኛ ትውልድ ወይም 5G ኔትወርክ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል። እንዲሁም ይህ አዲስ ስልክ 8 ጌጋ ባይት ራም እና 256 ጌጋ ባይት መጠን ያላቸው መረጃዎችን የመያዝ አቅም ሲኖረው ለተክም ሰዓት ማስጠቀም የሚያስችል ባትሪም አለው ተብሏል። ሶስት ካሜራ እንዳለው የተገለጸው ይህ አዲስ የቴክኖ ሞባይል ስልክ ካሳለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ ለደንበኞቹ ቀርቧል። ቴክኖ ሞባይል በትራንሽን ኩባንያ ስር ሆኖ በፈረንጆቹ 2006 ላይ የተመሰረተ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው። በጆርጁ ዙ የተቋቋመው ቴክኖ ሞባይል ዋና መቀመጫውን በቻይናዋ ሸንዘን አድርጎ በመላው ዓለም ምርቶቹን ለደንበኞቹ በማቅረብ…
Read More
በዓለም አቅፉ የአይሲቲ ውድድር ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ

በዓለም አቅፉ የአይሲቲ ውድድር ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ

ሁዋዌ ከግንቦት 16 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ባካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። በውድድሩ ከ36 አገሮች የተውጣጡ 146 ቡድኖች የተሳተፉ  ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ተማሪዎች  እያንዳንዳቸው ሶስት አባላት ያላቸው ሶስት ቡድን በመሆን በፕራክቲካል ትራክ (ዳታኮም፣ ሴኪዩሪቲ፣ WLAN፣ ቢግ ዳታ፣ ስቶሬጅ፣ AI፣ OpenEuler እና OpenGaussን ያካትታል) ሁለት ቡድን እና አንድ ቡድን በኢኖቬሽን ትራክ  ተሳትፈዋል። በኢኖቬሽን ትራክ የተወዳደሩት ተማሪዎች የራሳቸውን የፈጠራ ሃሳብ ይዘው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎቹ “የግእዝ ፊደላት ክላሲፋየር” የተሰኘ መወዳደሪያ ይዘው ቀርበዋል፡፡ የሁዋዌ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ሊዩ ጂፋን ተማሪዎቹ ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን ገልጸው ድርጅቱ…
Read More
ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ

ሩሲያ እና ቻይና አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቻቸው ለማስተማር ወሰኑ የዓለማችን ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ እና ብዙ ህዝብ ያላቸው ሩሲያ እና ቻይና የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ ለዜጎቻቸው እንዲሰጥ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ሩሲያ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በሞስኮ በሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጻለች፡፡ ትምህርቱ ከቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሳምንት ሁለት ክፍለ ጊዜ እንደሚሰጥ በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዋ አማርኛ ቋንቋን ለዜጎቿ ለማስተማር የወሰነችው ሀገር ቻይና ስትሆን ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም አማርኛን ለቻይናዊያን ተማሪዎች ለማስተማር የሚያግዘው መጽሀፍ በቤጂንግ…
Read More
ኢትዮጵያ በሼንዘኑ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ላይ በዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ትወከላለች

ኢትዮጵያ በሼንዘኑ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ላይ በዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ትወከላለች

የቻይናዋ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሼንዘን ከተማ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድርን ከግንቦት 16 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ታስተናግዳለች፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ወደ ቻይና ያቀኑ ሲሆን ለተወዳዳሪዎቹ የአሸኛኘት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ ውድድሩን ህዋዌ ያዘጋጀው ሲሆን በየሀገሩ በተካሄደ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ተማሪዎቹ በዚህ  ዓለም አቅፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ያቀኑት የተለያዩ ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው በየደረጃው በአሸናፊነት በማጠናቀቃቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያን በዚህ ውድድር ላይ የወከሉት ዘጠኙ ተማሪዎች  የተገኙት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ዋቸሞ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ነው። በውድድሩ ተማሪዎቹ  እያንዳንዳቸው ሶስት አባላት ያላቸው ሶስት ቡድን…
Read More
የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ እዳ 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ባንኮች የተበደረችውን ሳይጨምር ከውጭ አበዳሪ ምንጮች ተበድራ ያልመለሰችው የዕዳ መጠን 28 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል። እንደ ሚኒስቴሩ ሪፖርት ከሆነ ኢትዮጵያ ካለባት 28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ 54 በመቶ የተገኘው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡ 46 በመቶው ደግሞ ከቻይና እና ከሌሎች ውጭ የግል አበዳሪ ተቋማት የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ባለባት ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ብድር ምክንያትም በዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ምደባ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ያለባቸው አገሮች ዝርዝር ውስጥ ተመድባለች። በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት የቡድን 20 አገሮች የዕዳ ጫናን ለማቅለል ባዘጋጁት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ሥርዓት ለመጠቀም…
Read More
የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ ከሚያቀርብ የቻይና ቴክስታይል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ አቅርቦት ከቻይናው ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል። የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለሠራተኞች እንዲቀርብ የሚያስችል ውይይት ከጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተመላክቷል፡፡ ለደንብ ልብስ አቅርቦቱ ባንኩ ከፍተኛ ወጪ በመመደብ ለአብዛኛው ሠራተኛ ወጪውን የሸፈነ ሲሆን፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ የተወሰነ ወጪ ተጋርተው የሚቀርብ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ የጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ጋዊ ቻንሁሀ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ደንብ ልብስ ተቋማቸው በኢትዮጵያ ቅርንጫፉ ከሚሰራቸው አቅርቦቶች ትልቁ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ። አየር መንገዱ ወደ ሻንግሀይ ከተማ የካቲት 1973 የመጀመሪያ የቻይና በረራውን በማድረግ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን ከጥቅምት 1973 ጀምሮ ደግሞ መዳረሻውን ወደ ቤጂንግ ከተማ በመቀየር አገልግሎን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ5 የመንገደኛ እና 9 የእቃ ጭነት መደበኛ በረራዎች በአጠቃላይ 66 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ 10 የቻይና ከተሞች በማድረግ ላይ ይገናል። ቤጂንግ፣ ጓንዡ፣ ሼንጁ፣ሻንግሀይ፣ ሸንዘን ፣ ውሀን፣ቻንግሻ፣ዢያመን፣ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበርባቸው የቻይና ከተሞች ናቸው። የአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። በ1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 70ኛ የምስረታ በዓሉን ከአንድ ዓመት በፊት…
Read More
ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች። የትምህርት እድሉ ከ5 አመታት በፊት የተጀመረው የ "ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል" ነው።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው። በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ6 ተማሪዎች የሶስተኛ ዲግሪ፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ ለ12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላርሺፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ የተሰጠው የትምህርት እድል 2 ነጥብ 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል። የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደው ስነስርዓት…
Read More