Shenzhen

ኢትዮጵያ በሼንዘኑ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ላይ በዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ትወከላለች

ኢትዮጵያ በሼንዘኑ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ላይ በዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ትወከላለች

የቻይናዋ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሼንዘን ከተማ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድርን ከግንቦት 16 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ታስተናግዳለች፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ወደ ቻይና ያቀኑ ሲሆን ለተወዳዳሪዎቹ የአሸኛኘት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ ውድድሩን ህዋዌ ያዘጋጀው ሲሆን በየሀገሩ በተካሄደ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ተማሪዎቹ በዚህ  ዓለም አቅፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ያቀኑት የተለያዩ ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው በየደረጃው በአሸናፊነት በማጠናቀቃቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያን በዚህ ውድድር ላይ የወከሉት ዘጠኙ ተማሪዎች  የተገኙት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ዋቸሞ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ነው። በውድድሩ ተማሪዎቹ  እያንዳንዳቸው ሶስት አባላት ያላቸው ሶስት ቡድን…
Read More