AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ 150 ሺህ ዶላር የሚያወጡ ድጅታል ብሬሎችን ተረከበ

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ 150 ሺህ ዶላር የሚያወጡ ድጅታል ብሬሎችን ተረከበ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዘመናዊ ዲጂታል ብሬሎችን መረከቡን ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኮሪያው ሴሎም ኢንተርናሽናል ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረትም እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዲጂታል ብሬሎችን እንደተረከበ አስታውቋል፡፡ ዩንቨርሲቲው እንዳስታወቀው በቀጣይ ደግሞ ተመሳሳይ ቀሪ 30 ብሬሎችን በድጋፍ እንደሚረከብ ገልጿል። ይህ ዘመናዊ መሳሪያ ማየት የተሳናቸው  የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከወረቀት ብሬል ተላቀው በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚረዳ ሲሆን፤ ከተለያዩ ዳታቤዞችም ጥናታዊ ጽሑፎችን ያለምንም ክፍያ አውረደው መጠቀም ያስችላቸዋል ተብሏል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ለዲጂታላይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባ…
Read More
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስትሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው። በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና…
Read More
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶችን አሸነፈ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶችን አሸነፈ

የአውሮፓ ህብረት ከሚደግፋቸው አስራ ሰባት (17) የምርምር እና የትምህርት ልህቀት ማዕከላት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘጠኙ አሸናፊ ሆነ። ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ውጤት በመጪው ጥቂት ወራት የሚታወቅ ይሆናል ተብሏል። በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በ2022 November የARUA እና Guild የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በነበራቸው ስብሰባ በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ የምርምር እና የ ትምህርት ልህቀት ማእከላት ለማቋቋም ወስነው መለያየታቸው ይታወሳል። በዚሁ መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ፕሮፖዛሎች የቀረቡ ሲሆን ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ግምገማ መሰረት 17 የልህቀት ማእከል ተመስርተዋል። ከነዚህ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክቶች ውስጥም በዘጠኙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊ ሆኗል። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቶቹን በማሸነፉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ የሚያገኝ ይሆናል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት…
Read More
ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች። የትምህርት እድሉ ከ5 አመታት በፊት የተጀመረው የ "ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል" ነው።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው። በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ6 ተማሪዎች የሶስተኛ ዲግሪ፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ ለ12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላርሺፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ የተሰጠው የትምህርት እድል 2 ነጥብ 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል። የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደው ስነስርዓት…
Read More