26
Jun
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዘመናዊ ዲጂታል ብሬሎችን መረከቡን ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኮሪያው ሴሎም ኢንተርናሽናል ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረትም እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዲጂታል ብሬሎችን እንደተረከበ አስታውቋል፡፡ ዩንቨርሲቲው እንዳስታወቀው በቀጣይ ደግሞ ተመሳሳይ ቀሪ 30 ብሬሎችን በድጋፍ እንደሚረከብ ገልጿል። ይህ ዘመናዊ መሳሪያ ማየት የተሳናቸው የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከወረቀት ብሬል ተላቀው በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚረዳ ሲሆን፤ ከተለያዩ ዳታቤዞችም ጥናታዊ ጽሑፎችን ያለምንም ክፍያ አውረደው መጠቀም ያስችላቸዋል ተብሏል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ለዲጂታላይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባ…