18
Oct
በኢትዮጵያና በኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የ10 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በኮሪያ ሪፐብሊክ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ መካከል የኢትዮጵያ የጥራት አመራር አቅም ማጎልበቻ ፐሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የግብርና እና የተቀናበሩ የግብርና ምርት ውጤቶች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን ለዚህም ደቡብ ኮሪያ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች ተብሏል፡፡ በፊርማ ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሚስተር ሃን ዲዩግ ቾ እንደገለፁት የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ ግንኙነት ታረካዊ ነው ያሉ ሲሆን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ከ6000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለኮሪያ ህዝብ ተዋግተው የደም ዋጋ የከፈሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የፕሮጀክት ስምምነቱ የኮሪያ እና የኢትዮጵያ ወዳጅነትን…