11
Apr
በቻይና በሲሚንቶ ዘርፍ የተሰማራው ግዙፉ ሲኖማ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ መገንባት እንደሚፈልግ ገልጿል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የሲኖማ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ሊቀመንበር እና የሲኤንቢኤም ተቋም ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ሉ ያን እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል። ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስት በሚደረግበት ዙሪያ ቤጂንግ በሚገኘው የኩባንያው ዋና ጽ/ቤት ተገኝተው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ተፈራ በውይይቱ ወቅት ኩባንያው በኢትዮጵያ ባሉት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከዲዛይን ጀምሮ በግንባታ ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በኢትዮጵያ ካለው የግንባታ ስፋት አንጻር የሲሚንቶ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። አምባሳደር ተፈራ አያይዘውም፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ቢሰማራ የጋራ ተጠቃሚነቱ ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል።…