Chinaethiopia

የቻይና ኩባንያዎች ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል ፈጥረዋል ተባለ

የቻይና ኩባንያዎች ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል ፈጥረዋል ተባለ

ኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከሳበችው ውስጥ ግማሹ በቻይናዊን የተያዘ እንደሆነ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከቻይና ንግድ ምክር ቤት እና ከቻይና ኢምባሲ ጋር በአዲ አበባ ተወያይተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዚህ ጊዜ እንደገለጸው ባለፉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ ከተጀመሩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 50 በመቶ የሚሆኑት በቻይና ባለሀብቶች የለሙ ናቸው፡፡ ውይይቱ የቻይና ባለሀብቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ሲሆን ውይይቱ ለቻይና ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢን ለመፍጠር እና ተጨማሪ ባለሀበቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ አሁን ላይ ቻይና በኢትዮጵያ ከ 3 ሺህ 300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀከቶችን በማልማት ላይ ናት የተባለ ሲሆን ቻይና በኢትዮጵያ ከ325 ሺህ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድሎች ፈጥራለችም ተብሏል፡፡ ከሶስት ወራት በፊት…
Read More