04
Apr
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ። አየር መንገዱ ወደ ሻንግሀይ ከተማ የካቲት 1973 የመጀመሪያ የቻይና በረራውን በማድረግ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን ከጥቅምት 1973 ጀምሮ ደግሞ መዳረሻውን ወደ ቤጂንግ ከተማ በመቀየር አገልግሎን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ5 የመንገደኛ እና 9 የእቃ ጭነት መደበኛ በረራዎች በአጠቃላይ 66 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ 10 የቻይና ከተሞች በማድረግ ላይ ይገናል። ቤጂንግ፣ ጓንዡ፣ ሼንጁ፣ሻንግሀይ፣ ሸንዘን ፣ ውሀን፣ቻንግሻ፣ዢያመን፣ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበርባቸው የቻይና ከተሞች ናቸው። የአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። በ1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 70ኛ የምስረታ በዓሉን ከአንድ ዓመት በፊት…