20
Mar
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አምስት ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ። አሁን ላይ አየር መንገዱ 136 ዓለም አቀፍ እንዲሁም 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት የጠቆሙት ስራ አስፈጻሚው ተጨማሪ የአገር ውስጥ መዳረሻዎችን ለማስፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አምስት የአገር ውስጥ መዳረሻ ኤርፖርቶችን እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል። ኤርፖርቶቹ የሚገነቡት በሚዛን ቴፒ አማን፣ ያቤሎ፣ ጎሬ፣ መቱና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውን ገልጸው፤ አራቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል። ይህም በአገር ውስጥ ያሉ ደንበኞች ፍላጎት ተከትሎ የሚተገበር መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ሌሎች መዳረሻዎችን ጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ ግንባታቸው እንደሚቀጥል ተገልጿል። በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት…