28
Oct
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከፓርላማ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ከኤርትራ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት በአንድ ጀምበር የመጣ ሳይሆን ቀስ በቀስ በሂደት መምጣቱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመት በፊት የባህር ሀይሏን እንዳቋቋመች የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ ሀይል የተቋቋመው በሀገር ውስጥ ብቻ እንዲገታ በማሰብ አልነበረም አሰብ ወደብን ከኤርትራ እንደምንረከብ በማመን ነበር ብለዋል። "ከኤርትራ መንግሥት ጋር ተስማምተን ከዚህ ወደ አሰብ የሚወስደውን መንገድ ጠግነናል ፣እንከፍታለን ብለን ጠግነናል፣ መንገዱን ከጠገንን በኋላ ግን ችግር አለብን አሰብ ወደብ ተዳክሟል አሉን። አንዳንድ ሰው ከኤርትራ ጋር የገባንበት አለመግባባት በአንድ ምሽት የመጣ ይመስለዋል እንደዛ አይደለም ታሪኩን ስለማንናገር ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ። ወደ አሰብ መንገድ ጠግነን ከጨረስን በኃላ '…