15
Mar
በቱኒዚያ በተካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ የክፍለ አህጉራዊ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ክፍለ አህጉራዊ የፍጻሜ ውድድር ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በቱኒዚያ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት መካከል በኮምፒውቲንግ ትራክ (Computing Truck) የተወዳደሩት የሶስት ተማሪዎች ቡድን ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል። በጠቅላላ ውድድሩ ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የተውጣጡ 90 ተማሪዎች በተለያየ የውድድር ዘርፍ ተሳታፊ ሆነዋል። በውድድሩ ሶስተኛ ደረጃን የያዙት ተማሪዎች የሁዋዌን ዘመናዊ ስልክ የተሸለሙ ሲሆን የተቀሩት 6 ተማሪዎች በተሳትፏቸው የሁዋዌ ታብሌቶችን ተሸልመዋል። ኩባንያው ለተማሪዎቻቸው ድጋፍ ላደረጉ መምህራንም እውቅና ሰጥቷል። እነዚህ ሦስት ተማሪዎች ሁለቱ…