14
Jan
ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ የ2025 ሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደር ሆና ተመርጣለች፡፡ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓመታዊ የስልጠና መርሃ ግብር፣ ከሁዋዌ ታዋቂ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የ2025 የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር አለም አቀፍ አምባሳደሮችን መርጦ አሳውቋል። ከተመረጡት 12 አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኽሊፋ ትገኛለች። ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓላማውን ያደረገው በዓለም ዙሪያ ያሉ ወጣት ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን አረዳዳቸውን ማሳደግ ነው። ለዚህም አጫጭር ስልጠናዎችን፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እና የተመራቂዎች ማህበር እንቅስቃሴዎች (አልሙናይ) ተሳትፎ እንዲጎለብት ይሰራል። የባህል ልውውጦች አስፈላጊነት እና የስራ ፈጣሪነት…