10
Jul
የኢትዮጵያ ቡድን በሞሮኮ በተካሄደው የሁዋዌ ቴክ ፎር ጉድ ክፍለ አህጉራዊ ውድድርን በአንደኝነት አጠናቋል፡፡ የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር “Huawie Seeds for the Future 2024” የቴክኖሎጂ ስልጠና መርሃ ግብር በሞሮኮ (ኢሳዉራ) ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል። ይህ ስልጠና ከምስራቅ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የተውጣጡ 17 አገራትን አሳትፏል። ኢትዮጵያም ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 10 ተማሪዎችን በስልጠናው ያሳተፈች ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 5 ተማሪዎችን የያዘው የኢትዮጵያ አንድ ቡድን በሁዋዌ ቴክፎርጉድ ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸንፏል፡፡ ተማሪዎቹ በቴክ ፎር ጉድ ክፍለ አህጉራዊ (ግሎባል) ፕሮጀክት ከመወዳደራቸው በፊት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን ወስደዋል። ተሳታፊ ተማሪዎቹ በ28 ቡድኖች ተከፋፍለው ለውድድር የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ያዘጋጁ…